አፍሪካን መስማት


በብርቱ መፍትሔዎች ሕይወትን ለዘላቂው ስለመለወጥ

የዝናብ እንጥብጥብታ ፤ የጓደኞች ሣቅ፣ ጨዋታ ፤ የቤተ-እምነት ዝማሬ ፤ የእናት የፍቅር ድምፅ፣ የልብ ወሬ። በእነዚህና በመሳሰሉ ኣያሌ ድንቅ ድምፀቶች የተሞላች ነች፣ ዓለም።

ነገር ግን በሚያሳዝን መልኩ ሁሉም ሕፃናት እነዚህን ቅላፄዎች ለመስማት አልታደሉም። ዕለት ከዕለት በርካቶች የሕይወትን ድምፀት ለማጣጣም ሳይቻላቸው ያልፋቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ሳይታወቅላቸው! ልጅዎት ላይ የመስማት እክል ይኖራል የሚል ሥጋት አለዎት?

ስለ የጆሮ የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት

የጆሮ የመስማት ዐቅም መድከም፣ ብሎም ሙሉ ለሙሉ ማጣት በአፍሪካ ዙርያ ባሉ ሕፃናት ላይ ባስደንጋጭ መልኩ የተበራከተ ክስተት ነው። የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት በርካታ መነሾዎች ሊኖሩት ይችላሉ። ማጅራት ገትር፣ የጆሮ ውስጥ መመርቀዝ፣ እንዲሁም ሌሎች የጤና እክሎች ከሚጠቀሱት መሀል ይገኙባቸዋል።

በአፍሪካ ምድር በግምት 8 ሚሊዮን ሕፃናት በከባድ የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት ይጠቃሉ
አፍሪካ ውስጥ በየዓመቱ ከ200 ሺህ በላይ ሕፃናት ከመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት ጋር ይወለዳሉ
በአፍሪካ ምድር ከመቶ ሕፃናት ሁለቱ ከባድ የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት አለባቸው

የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት ምልክቶች

ሕፃናት ላይ የመስማት ዐቅም የመድከም ወይም የማጣት ምልክቶችን መለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ልጅዎት ላይ የመስማት ዐቅም የመድከም ወይም የማጣት ችግር ይኖራል የሚል ሥጋት ካለዎት በተቻለ ፍጥነት በባለሞያ የመስማት ዐቅም ምዘና ማድረግ ጠቃሚ ይሆናል። ይህ ለልጅዎ ተገቢውን መፍትሔ ለመጠቆም ይረዳልና።

የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት ምልክቶች

መስማት የሚችሉ ሕፃናት፦

 • ለድምፀቶች አጸፋውን መግለጽ ይቻላቸዋል።
 • የተለመዱ ድምፆችን መለየት አያዳግታቸውም።
 • የራሳቸውን ድምፆች ማውጣት ይጀማምራሉ።
የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት ምልክቶች

ሁለት ዓመት እና ከዛ በላይ የሞላቸው መስማት የሚችሉ ሕፃናት፦

 • ቀላል ትእዛዞችን ለመቀበል አይቸገሩም።
 • የንግግር ቃላት መጠቀምን ይለማመዳሉ።
 • የንግግር ቋንቋን ይረዳሉ።
ድምፅ ላይ ነፍስ ስለመዝራት

ድምፅ ላይ ነፍስ ስለመዝራት

ሁሉም ሰው በድምፅ ያሸበረቀ ሕይወትን ሊኖር ይገባል የሚል ጽኑ እምነት አለን። ልጅዎት ላይ ከባድ የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት ቢኖር ተስፋ አይቁረጡ። ለጆሮ ውስጥ የመሣሪያ ተከላ ጥበብ ምስጋና ይግባውና በዓለም ዙርያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት የመስማት ችሎታ ሊመለስ ወይም “ሀ” ብሎ ሊጀምር በቅቷል። የጆሮ ውስጥ ተከላ ያካሄዱ ሕፃናት መስማትና መናገር ይችላሉ፣ በትምህርታቸውም ላይ መሻሻል ያሳያሉ። በስፖርት እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፋሉ፣ ሙዚቃን ያጣጥማሉ፣ ከሕይወት ድምፀትም ይቋደሳሉ።

 

ለመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት መፍትሔዎች

የጆሮ ውስጥ የመሣሪያ ተከላ የረቀቀ የሕክምና ጥበብ ነው። ከአጋዥ ማድመጫ መሣሪያዎች የተለየና የከፉ የመስማት ዐቅም የመድከም ወይም የማጣት ችግሮችን ጭምር ለማስተካከል የሚረዳ ጥገናዊ የሕክምና መፍትሔ ነው። የመሣሪያ ተከላው የልጅዎ ተፈጥሮአዊ የማድመጫ ሥርዓት ላይ ውስጥ ለውስጥ የሚቀጠል ዓይነት ሥሪት አለው። ይህ አወቃቀሩ በተፈጥሮ የመስማት ሂደት ላይ እልክ የፈጠረውን የጆሮ አካል (ጥምዜ ተብሎ የሚጠራውን) ወደ ጎን በመተው፣ ተላልፎት እንዲሠራ ያስችለዋል።

Hearing Africa EAR1 2

የጆሮ ውስጥ መሣሪያ ትክል ሁለት አካላት አሉት፦

 1. የመጀመሪያው የልጅዎ የጆሮ ግንድ ላይ የሚለጠፍ የድምፅ አሰላሳይ / አቀናባሪ እና የተቀባይ ማይክሮፎን ቅንጣት መሣሪያዎች ውሕድ ሲሆን፣
 2. ከውስጠኛዎቹ የጆሮ አካላት ጋር የሚገናኘውና ቆዳ ሥር የሚገባው ትክል ሁለተኛው መሣሪያ ነው።

ድምፅ አሰላሳዩ / አቀናባሪው ከማይክሮፎኑ የሚቀበለውን ድምፅ ያነብና ወደ ትክሉ ያስተላልፈዋል። ትክሉም የተቀበለውን ሲግናል ወደ ድምፅ የሚቀይር ቴክኖሎጂን በመጠቀም መሰማት በሚችል መልኩ ለልጅዎ ያደርሰዋል።

የጆሮ ውስጥ መሣሪያ ትክል እንዴት እንደሚሠራ ይመልከቱ

ስለ የልጅዎ የጆሮ ውስጥ መሣሪያ ትክል ተጨማሪ ያንብቡ

የተጠቃሚዎች ምስክርነት

ወላጆቻቸውን ከመስማት ጀምሮ ከጓደኞቻቸው ጋር እስከመጫወት ባሉ ገጽታዎች የጆሮ ውስጥ መሣሪያ ተከላ እንዴት የልጆችን፣ ብሎም የቤተሰቦቻቸውን ሕይወት እንደቀየረ ይመልከቱ።

ቀጣይ እርምጃዎች

የአንድ አባሉ የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ሙሉ በሙሉ ማጣት ለመላው ቤተሰብ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል እንገነዘባለን። ስለሆነም በዚህ ዓይነቱ የሕይወት ጎዳና ላይ እገዛ ልናደርግልዎ እዚህ እንገኛለን።

ለመስማት ዐቅም መድከም የሚደረግ የሕክምና ሂደት ምን ይመስላል?

 • በቅድሚያ ወደ የሥነ-ድምፀት ባለሞያ ጎራ በማለት ለልጅዎ የመስማት ዐቅም ምዘና ማድረግ ይኖርቦታል። ይህ ለልጆዎ ተስማሚውን መፍትሔ ለመለየት ያስችሎታል። በአቅራቢያዎ የሚገኝ ባለሞያ ለማግኘት ልናግዝዎም እንችላለን። በዚህ ድረ ገጽ በስተመጨረሻ የተቀመጠውን ቅፅ መሙላት ብቻ ነው የሚጠበቅብዎት።
 • ለልጅዎ ተስማሚው መፍትሔ የጆሮ ውስጥ መሣሪያ ተከላ ሆኖ ከተገኘ ቀጣዩ እርምጃ ተከላውን ማካሄድ ይሆናል። ይህ ቀላልና ያልተወሳሰበ የቀዶ ጥገና ዓይነት ነው። እንደ ሐኪምዎ ውሣኔ የልጅዎ የሆስፒታል ቆይታ ከአንድ ወይም ከሁለት ቀናት ላልበለጠ ጊዜ ብቻ ይሆናል።
 • ከተከላው በግምት ከአራት ሳምንታት በኋላ ትክሉ መሣሪያ ወደ ሥራ መግባት ይችላል። በዚህ ጊዜ የሥነ-ድምፀት ባለሞያዎ ትክሉን ከልጅዎ ፍላጎት ጋር ከማናበብ በተጨማሪ ስለአጠቃቀሙ መመሪያ ይሰጥዎታል። መሣሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ ለልጅዎ እንደ አዲስ ጆሮ ድምፆችን ማንቆንቆር የሚጀምረውም በዚህ ቅፅበት ነው።
 • ትክሉ መሣሪያ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ ልጅዎን ከነዚህ አዳዲስ የድምፅ ዓለማት ጋር ማላመድ ያስፈልጋል። ስለሆነም የዕለት ከዕለት የማዳመጥ ልምምዶች ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህንንም ከሥነ-ድምፀት ባለሞያ ጋር ወይም በመኖሪያ ቤትዎ ውስጥ ማድረግ ይችላል።

የሥነ-ድምፀት ባለሞያ ስለማግኘት

ከመስማት ዐቅም መድከም ወይም ሙሉ ለሙሉ ማጣት ጋር በተያያዘ ሳይረፍድ መታከም ለውጤታማነት ወሳኝ ነው። ልጅዎት ላይ የመስማት ዐቅም መድከም ወይም ማጣት ይኖራል የሚል ጥርጣሬ ካለዎት በተቻለ ፍጥነት በባለሞያ የመስማት ችሎታ ምዘና ቢያደርጉ ይመከራል።

ከታች የሚገኘውን ቅጽ ሞልተው ቢልኩልን በአቅራቢያዎ የሚገኝ የሥነ-ድምፀት ባለሞያ በማፈላለግ ልናግዝዎ ዝግጁ ነን።

ስልክ ቁጥር